በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን
ቤተክርስቲያናችን በእግዚአብሔር የተወደደውን አገልግሎቷን ስትፈጽም እግዚአብሔር ለባህርዩ ቆሻሻ ነገር አይስማማውምና እንደ አቤል ለተወደደው መስዋዕቷ ማቅረቢያ ለአገልገሎቷም ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ ንዋያተ ቅድሳቷን እንደየ ሥርዓቱ አዘጋጅታለች፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
1. ታቦት /ark/፡- ማለት ማደሪያ ማለት ነው ማደሪያነቱም ለልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታ ሙሴን ሸምሸርሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቱን 125 ቁመቱን 75 ወርዱን 75 ሳ.ሜ አድርገህ
ታቦትን ቅረጽ በውስጥና በውጭ በወርቅ ለብጠው፣ ሁለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አስመስለህ ቅረጽበት ብሎ አዝዞት እንዳለው አድርጎ ሠርቶታል በአገልግሎት ረገድም የጽላቱ ማኖሪያና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር ዘጸ 25፣1-22፣ 40፣20
እስራኤል ታቦትን ያከብሩ ጌታም በርሱአድሮ ብዙ ተአምራትን ያድርግላቸው ነበር ኢያሱ 3፣6 ሳሙ 4፣6 ዛሬም በቤተ መቅደስ መሥዋዕተ ወንጌል የጌታ ሥጋና ደሙ ይፈተትበታል፡፡
ምሳሌነቱም፡- ታቦት የእመቤታችን ፣ጽላት የጌታ ፣አንድም ታቦት የእመቤታችን ፣ጽላት የትስብዕት /የሥጋ/ ቃሉ የአካላዊ ቃል ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ታቦት የጌታ ፣የማይነቅዝ እንጨት የእመቤታችን ምሳሌ፤ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቱ ጌታ በኃጢአት ከማትለወጥ ከእመቤታችን ለመወለዱ ምሳሌ ነው፡፡
2. ጽላት /Tablet of the law/፡- ጽላት ማለት ሰሌዳ አንድም መጸለያ ማለት ነው የመጀመሪያዋ ጽላት በግብር አምላካዊ የተገኘች 2 ክፍሎች ያሏትና 10ሩ ትእዛዛት የተጻፈባት ሙሴ በደብረ ሲና ከጌታ የተቀበላት ኋላም እስራኤል ለጣኦት ሲሰግዱ አይቶ ቢደነግጥ ከእጁ ወድቃ የተሰበረችው የዕንቁ ጽላት ናት ዘጸ 32፣15-20
ሁለተኛዋ ሙሴ በፊተኛዋ አምሳል መሠረት በግብር አምላካዊ 10ሩ ትዕዛዛት የተጻፈባት በቤተ መቅደስ በታቦቱ ላይ ሆና ኃይል ታደርግ የነበረችና /ዘጸ 34፣1-28/ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ወደ ሀገራችን
መጥታ በአክሱም ጹዮን እንደተቀመጠች የሚነገርላት የዕብነበረድ ጽላት ናት፡፡ ምሳሌነቷ ከላይ ተገልጿል ጸሎተ ቅዳሴው ታቦቱንና ጽላቱን አንድ አድርጎ ታቦት እያለ ይጠራዋል፡፡
3. መንበር /Throne/፡- ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት ወይም ከእንጨት ይሠራል አገልግሎቱም ከቤተ መቅደስ ታቦት /ጽላት/ ይቀመጥበታል ጸሎት ይጸለይበታል መሠዋዕት ይሠዋበታል በመንበሩ ላይ በመደበኛነት የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት ታቦት /ጽላትና/ ሥዕለ ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ ሲሆኑ
በቅዳሴ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ለመፈተት የምንገለገልባቸው ጻሕል ፣ጽዋዕ ፣ማኀፈዳት፣ ዕረፈ መስቀል ፣መስቀል ፣ዕጣን ይቀመጡበታል፡፡
መንበሩን የሚዳስሱና የሚያገለግሉበት ቀሳውስቱ ናቸው ዲያቆናት ግን ከበውት ይቆማሉ፡፡
ምሳሌነቱም፡- መንበር የእመቤታችን ፣ታቦት /ጽላት/ የጌታ ፣አንድም መንበር የመንበረ ጸባዖት፣ ታቦት /ጽላት/ የሰማያዊ ንጉሥ የጌታ፣ ልዑካን የሠራዊተ መላእክት ምሳሌ፡፡
4. አትሮንስ /Lectern/፡- በመንበሩ አጠገብ ይቆማል ቄሱ የሚጸልይበትን መጽሐፈ ቅዳሴ ያስቀምጥበታል
ምሳሌነቱ፡- አትሮንስ የጌታ ዙፋን ፣መጽሐፍ የጌታ አንድም አትሮንስ የእመቤታችን መጽሐፍ የጌታ ምሳሌ ነው፡፡
5. አልባሰ ቅዳሴ /Cloths of service/፡- ልዑካን ሥጋውን ደሙን በመፈተት ጊዜ የሚለብሱት የአገልግሎት ልብስ ቁጥሩ ከንዋያተ ቅድሳት ነው፡፡ የዚህ ልብስ ሥርዓት መሠረቱ ጌታ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አሮን ይለብሰው የነበረው ከሰማያዊ ፣ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሀት የተሠራና 12 የወርቅ ሻኩራዎች ያሉት የተቀደሰው ልብስ ነው ዘጸ 39፣1-25 አሮን ይህንን ልብስ ለብሶ ወደ መቅደስ ሲገባ ከሻኩራዎች ድምፅ ይሰማ በድምፁም ምክንያት ሕዝቡ ከደዌያቸው ይድኑ ነበር ዘጸ 28፣35 ፡፡
ምሳሌነቱ፡- ልብስ የንጹሃን አበው፣ የወርቅ ሻኩራ የእመቤታችን ፣ድምፅ የጌታ ምሳሌ፣ ከሻኩራው በሚሰማ ድምጽ ሕዝቡ ከደዌያቸው መዳናቸው ከእመቤታችን በተወለደ በጌታ ዓለም ሁሉ የመዳኑ ምሳሌ ነው፡፡
· ለቅዳሴ የሚመረጠው ነጭ ልብስ ነው “ወአልባሰ ቅዳሴ እለ ይቄድሱ ቦቶን ይኩና ፀዐድወ ወአኮ ኅብራተ” እንዲል ቀኖና ሲለበሱም አስቀድመው የሚሆናቸውን አይተው ኤጲስ ቆጶስ ካለ በርሱ ከሌለም በካህኑ አስባርከው ይለብሳሉ የለበሱትን አውልቆ ሌላ መልበስ አይገባም፡፡
6. አክሊሊ /Holy crown/፡- የኦሪት ካህናት ከጥሩ ወርቅ የተሠራና ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ቃል የተጻፈበት ማዕተብ ያለው የተቀደሰ አክሊል ያደርጉ ነበር ዘጸ 39፣3ዐ ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ልዑካኑ አክሊል የማድረጋቸው ሥርዓት ከዚህ ጋር የተያያዘ ሲሆን በአክሊሉ ላይ የሚቀረጸው ግን የተጠቀሰው ቃል ሳይሆን መስቀል ነው፡፡ ልዑካኑ ልብሰ ተክህኖ የሚለብሱት አክሊል የሚደፉት ስለሥጋና ደሙ ክብር ነው አክሊል የክብር ምልክት ነውና 1ቆሮ 9፣25
7. ጽንሓሕ /Censer/፡- የዕጣን ማጠኛ ማሻታቻ ነው፡፡ የኦሪት ጽንሓሕ -ሸምሸር ሸጠን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸና በወርቅ የተለበጠ 125 ሳ.ሜ ርዝመት ያለው ነበር ዘሌ 16፣12 ዕብ 9፣4 ዛሬ ግን ከንጹህ ወርቅ ማዘጋጀት የሚቻል ባለመሆኑ የሚሠራው ከብረት ወይም ከናስ ወይም የወርቅና የብር መልክ ካላቸው እሳት በቀላሉ ከማይጐዳቸው ማዕድናት ነው፡፡
8. ዕጣን /Incense/፡- ቅዳሴን ጨምሮ በሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ጊዜ የሚቀርብ መባዕ ነው በመሆኑም ንጹህና ነውር የሌለበት መዓዛው ያማረ ሊሆን ይገባል፡፡ ዘጸ 30፣35 ለእግዚአብሔር
የተመረጠውን መልካም ዕጣን ከመቅደስ ውጪ ለግል መጠቀም አልተፈቀደም ዘጸ 3ዐ፣37-38
9. መጻሕፍት /Sacred books/፡- በቅዳሴ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥባቸው መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ /መዝሙረ ዳዊት፣ ሐዲስ ኪዳን/ እና መጽሐፈ ቅዳሴ ናቸው ጸሎተ ዕጣንና ግጻዌም ድርሻ አላቸው፡፡
10. መስቀል /Cross/፡- በቅዳሴ ጊዜ ቀሳውስቱ የእጅ መስቀል ዲያቆን ባለመጾር መስቀል ይይዛሉ ጌታ በዕለተ ዓርብ መስቀሉን ተሸክሞ እየወደቀ አየተነሣ ቀራንዮ የመውጣቱ ምሳሌ ነው፡፡
11. መሶበወርቅ /Golden pot/፡- መሥዋዕት ማክበሪያ ነው ዲያቆን በራሱ ተሸክሞ መስዋዕቱን ከቤተልሄም ወደ መቅደሱ ያቀርብበታል፡፡
ምሳሌነቱ፡- መሶብ የእመቤታችን ፣ወርቅ የንጽህናዋ የቅድስናዋ፣ ኀብስቱ የጌታ ፣ዲያቆን የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ፣ ከቤተልሔም ወደ መቅደስ መምጣቱ ጌታ ነቢያት በተናገሩለት ትንቢት መሠረት በቤተልሐም ተወልዶ በቀራኒዮ የመሰዋቱ ምሳሌ ነው፡፡ በኦሪት የነበረች መሶበ ወርቅ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸች በወርቅ የተለበጠች ነበረች መናም ያስቀምጡባት ነበር ዕብ 9፣4 ፡፡
12. ጻሕል /Paten/፡- ከሸክላ ወይም ከናስ ከብረት ወይም ከወርቅ ከብር የሚሠራ ጐድጐድ ያለ ወጭት ነው በኦሪት ኅብስተ ገጽ ይቀርብበት ነበር ዛሬም ከመንበሩ ላይ ሆኖ የጌታ ሥጋ ይቀመጥበታል፡፡ የጌታ መቃብር ምሳሌ ነው፡፡
13. ጽዋዕ /Cup/፡- እንደ ጻሕሉ ከሸክላ ወይም ከከበረ ማዕድን ሊሠራ ይችላል የደሙ ማቅረቢያ ሲሆን የጌታ መቃብር አንድም መላእክት ከጌታ ጐን የፈሰሰውን ደም ተቀብለው በዓለም ሁሉ የረጩበት የብርሃን ጽዋ ምሳሌ ነው፡፡
14. ማኀፈድ /Covering cloth/፡- ከተመረጠ ጨርቅ የሚሠራ የሥጋውና የደሙ መሸፈኛ ነው 5 ማኅፈዳት አገልግሎት ይሰጥባቸዋል አንድ ጻሕሉ ላይ ይነጠፋል 3ቱ ኀብስተ ቁርባኑ ይሸፈንባቸዋል አንዱ የጽዋዕ መሸፈኛ ነው፡፡ የጌታ ሰበን ምሳሌ ነው፡፡
15. ተቅዋም-መቅረዝ /Lamp holder/፡- የመብራት መስቀያ ማስቀመጫ ነው በኦሪት ከማይ ነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በወርቅ የተለበጠ እንደ ጽዋዕ እግርና ሰባት ቅርንጫፎች ያሉት መቅረዝ ነበር በመካከለኛ የተቀዳው ዘይት በስድስቱ ሁሉ ይሞላ፣ መብራቱም ሙሉ ሌሊት ሲበራ ያድር ነበር ዘጸ 25፣31-40/27፣20 ዕብ 9፣2
ዛሬም በሐዲስ ያለው አገልግሎት ተመሳሳይ ነው ዘይት ሻማ ይበራበታል መብራቱ ከ2 ሊያንስ አይገባም፡፡
ምሳሌነቱ፡- መቅረዝ የእመቤታችን፣ መብራት /ብርሃን/ የጌታ፣ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ቅርንጫፎች የምእመናን ምሳሌ ፣ቅርንጫፎች 7 መሆናቸው የእመቤታችንን ፍጽምትነት ያጠይቃል ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ነውና “እስመ ኁልቆ ሳብዕ በኀበ ዕብራውያን ፍጹም ውእቱ” እንዲል ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአበሔር

እግዚአብሔር ይስጥልን
ReplyDeleteአገልግሎታችሁን ይቀበልላችሁ
እንዴት ደስ ይላል
ቃለ ህይወት ያሰማልን።
ReplyDeleteሰፊ ማብራሪያ ቢኖረው ደግሞ ይበልጥ....