Tuesday, September 17, 2013

የንዋያተ ቅድሳት ዓይነት አገልግሎትና ትርጉማቸው


 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ቤተክርስቲያናችን በእግዚአብሔር የተወደደውን አገልግሎቷን ስትፈጽም እግዚአብሔር ለባህርዩ ቆሻሻ ነገር አይስማማውምና እንደ አቤል ለተወደደው መስዋዕቷ ማቅረቢያ ለአገልገሎቷም ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ ንዋያተ ቅድሳቷን እንደየ ሥርዓቱ አዘጋጅታለች፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

1. ታቦት /ark/፡- ማለት ማደሪያ ማለት ነው ማደሪያነቱም ለልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታ ሙሴን ሸምሸርሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቱን 125 ቁመቱን 75 ወርዱን 75 ሳ.ሜ አድርገህ

፫ቱ ዛፎች


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
                    የአራዊት መጠለያ ከሆነው ጥቅጥቅ ካለው ደን መካከል ከፍ ብለው የሚታዩ ሦስት ዛፎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ዛፎች ካሉበት ሆነው እንዳች ጠቃሚ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ዛፎች ወደ ፊት ምን መሆን እንደሚፈልጉ የልባቸውን ምኞት በግልጽ እየተነጋገሩ ነበር፡፡

“አኔ መቼስ” አለ አንደኛው ዛፍ “ፈጣሪዬ ቢፈቅድና ከአናጺዎች ምሳር ቢሠውረኝ ምኞቴ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ ነው፡፡” አለ፡፡ ሁለተኛው ዛፍ በመገረም “ዛፍ ካልተቆረጠና ለአንድ ሥራ ካልዋለ ዝም ብሎ ቢቆም አርጅቶ ከመውደቅ ሌላ ምን ትልቅ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል” ብሎ ጠየቀው፡፡